የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በጎፋ ዞን ባሉ ስድስቱ ምርጫ ክልሎች የተደረገው የምርጫ ሂደት ከድምፅ አሰጣጥ ጀምሮ እስከ ድህረ ምርጫ ድረስ በሰላም፣ በቅንጅት እና በትብብር በመጠናቀቁ ለመላው የዞኑ ህዝብ እና ባለድርሻ አካላት ከልብ የመነጨ ምስጋና አስተላልፈዋል።
የጎፋና የኦይዳ ህዝብ የዲሞክራሲ ተሳትፎውን በተግባር በማሳየት ከማለዳው ጀምሮ እስከ ሌሊት ድረስ በትዕግስት፣ በቁርጠኝነት እና በኃላፊነት ስሜት ድምፁን በመስጠት ለምርጫው ስኬት የማይተካ አስተዋፅኦ ማድረጉን ገልጸዋል።
በተጨማሪም የምርጫ አስፈጻሚ አካላት፣ የጸጥታ ኃይሎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሚዲያ ተቋማት እና ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለተሳካው የምርጫ ሂደት ያደረጉትን ከፍተኛ ርብርብ አድንቀው አመስግነዋል።
"የጎፋና የኦይዳ ህዝብ ለሰላም፣ ለአንድነት እና ለዲሞክራሲ ያለውን ጽኑ አቋም በዚህ ምርጫ በግልጽ አሳይቷል። ይህ የተገኘው ሰላማዊ ድባብ ወደፊትም ለልማትና ለመልካም አስተዳደር ጠንካራ መሠረት ይሆናል" ብለዋል።
በመጨረሻም የጎፋ ዞን ህዝብ በምርጫው ወቅት ያሳየውን አርአያነት፣ ህግ አክባሪነት እና የሰላም ባህል በቀጣይም እንዲያስቀጥል ጥሪ በማቅረብ የምስጋና መልዕክታቸውን አጠናቀዋል።
የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ምስጋና አስተላልፈዋል