በጎፋ ዞን በዑባ ደብረፀይ ወረዳ የ26 ኪሎ ሜትር በቶ- ቦላ ባላ -ጋዶላ -ደብረፀሐይ ቀበሌ ፕሮጀክት የመንገድ ስራ በደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን የሣውላ ዲስትሪክት ስራአስክያጅ አቶ ድምሬ ድቤታ እንደገለፁት የመንገዱ ስራ በክልሉ የመንገዶች ባለስልጣን በሣውላ ዲስትሪክት እየተሰራ እንዳለ ተናግረው ከታቀደው 26 ኪሎ ሜትር ውስጥ 13.5 ኪሎ ሜትር የአፈር ቆረጣው ተሰርቷል በማለት ገልፀዋል።
አክለውም የቀጣይ ስራ እስከ ደብረፀሐይ ቀበሌ ለማስገባት በቁርጠኝነት ለማህበረሰብ ተጠቃሚነት የመንገዱን ጥራት በማስጠበቅ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
አያይዘውም የፕሮጀክቱ ስራ በቶ ኬንቾ ጳሊ ደብረፀሐይ በመባል በፕሮጀክት ስም የተያዘ ቢሆንም በአንዳንድ የአካባቢው የመሬት አቀማመጥ ችግር የዛሬው በቶ ቦላ ባላ ጋርዶላ ደብረፀሐይ ሳይቱን በቅየሳ በማሻሻል ለተጠቃሚነቱ በቁርጠኝነት እየተሰራ ቀጥሏል ብለዋል።
በዞኑ ውስጥ የሣውላ ዲስትሪክት በ6 ፕሮጀክቶች የመንገድ ግንባታዎች በትኩረት በጥራትና በፍጥነት እየተሰራ ነው በማለት ገልፀው ድስትሪክቱ በዞኑ መገኘቱ ለማህበረሰቡ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ስሉም ተደምጠዋል።
የዑባደብረፀሐይ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ትዕዛዙ ሀጳ በበኩላቸው ከበቶ ጀምሮ ቦላ ባላን ይዞ እስከ ደብረፀሐይ ቀበሌ ድረስ እየተሰራ ያለው መንገድ የማህበረሰባችን የዘመናት ጥያቄ ነው በማለት ገልፀዋል።
አያይዘውም የዚህ መንገድ መሰራት ከ10 በላይ ቀበሌያት ተጠቃሚ የሚያደርግ ስሆን እንደመንግስት የቅርብ ክትትል እየተደረገ እንዳለና የማህበረሰባችን ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ የቀደሙ ችግሮችን እንደሚፈታ ተናግረዋል።
የዑባ ደብረፀሐይ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ አቶ መሪነህ ማዛራ በበኩላቸው እንደተናገሩት ፓርቲያችን ብልፅግና ሰው ተኮር ፓርቲ መሆኑና የጀመራቸውን ልማቶች እንደሚጨርስ የዚህ መንገድ ግንባታ ማሳያ ይሆናል በማለት ገልፀዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ሣውላ ዲስትሪክት የመንገዶች ጥገና አስተባባሪ አቶ ስለሽ ሽብሩ እንደገለፁት በድስትሪክቱ በመሰራት ላይ ከሚገኙ 6 የመንገድ የፕሮጀክት ስራዎች የበቶ ቦላ ባላ ጋርዶላ ደብረፀሐይ የመንገድ ግንባታ አንዱ ሲሆን 26 ኪሎ ሜትር እንደሚሸፍን ተናግረው የአፈር ቆረጣ ስራ 13.5 ኪሎ ሜትር እንደተሰራ ገልፀዋል።
አያይዘውም በቀጣይ የድልድይና የስትራክቸር ስራዎችን በማጠናቀቅ በቅርብ ጊዜ ለማህበረሰቡ አገልግሎት ክፍት እንደሚደረግ ተናግረዋል።
የበቶ ቦላ ባላ ደብረፀሐይ ቀበሌ ፕሮጀክት አስተባባሪ አለማዬሁ ሙሉጌታ እንደተናገሩት የ26 ኪሎ ሜትር በቶ ቦላ ባላን ጋዶላ ደብረፀሐይ እየተሰራ ያለ 13 ኪሎ ሜትር የአፈር ቆረጣውን በ45 ቀን ውስጥ በመጨረስ ወደ ስትራክቸር ስራ ይገባል በማለት ገልፀዋል።
አያይዘውም መንገዱን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ በርብርብ እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።
አንዳንድ ያነጋገርናቸው የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያዬት ከዚህ ቀደም መንገድ ባለመኖሩ ብዙ ወገኖችን ለህክምና ለማድረስ ባለመቻሉ ህይወታቸውን እንዳጡ ገልፀው የዚህ መንገድ መሠራት ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ይፈታልናል በማለት ተናግረዋለሰ።
በዑባ ደብረፀይ ወረዳ የ26 ኪሎ ሜትር በቶ -ቦላ ባላ -ጋዶላ -ደብረፀሐይ ቀበሌ ፕሮጀክት የመንገድ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።