የጎፋ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ዘመናዊ ድህረ ገጽ አበልጽጓል!

የጎፋ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ወቅታዊ፣ ተዓማኒ እና ተደራሽ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ በፍጥነት ለማድረስ በማሰብ በተቋሙ ስም ዘመናዊ ድህረ ገጽ አበልጽጓል።

ድህረ ገጹ በዞኑ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች፣ የመንግስት ፖሊሲዎች፣ የአመራር ውሳኔዎች፣ የህዝብ ተሳትፎ መርሃ ግብሮች እና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን በወቅቱ ለህብረተሰቡ የሚያደርስ መድረክ ሆኖ ያገለግላል።

በዲጂታል ቴክኖሎጂ የተደገፈው ይህ ድህረ ገጽ የመንግስትና የህብረተሰብ ግንኙነትን ለማጠናከር፣ ግልጽነትን ለማስፈን እና ትክክለኛ መረጃን ለማሰራጨት የሚያግዝ ነው።

ህብረተሰቡ የዞኑን ወቅታዊ ክንውኖች፣ የልማት ስኬቶች እና ጠቃሚ መረጃዎችን በድህረ ገጹ በመከታተል ተደራሽ እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።