በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ሣውላ ዲስትሪክት በጎፋ ዞን የሜላ -ጵዝጎ -ዳማ- ቆርጳ -በቶ የመንገድ ሰራ በፍጥነት እየተሰራ ይገኛል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ሣውላ ዲስትሪክት በጎፋ ዞን የሜላ -ጵዝጎ -ዳማ -ቆርጳ - የመንገድ ሰራ በፍጥነት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በዚህም የሎት አንድ የሜላ -ጵዝጎ የ23 ኪ/ሜ የመንገድ ግንባታ ስራን በተያዘለት የጊዜ ሰለዳ በጥራት ለማጠናቀቅ ባለስልጣኑ ልዩ ክትትል እና ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ሣውላ ዲስትሪክት ስራ አስክያጅ አቶ ድምሬ ድበታ እንደተናገሩት ዲስትሪክቱ ከሚያሰራቸው የመንገድ ግንባታዎች ውስጥ አንዱ የሆነው ከሜላ የተጀመረው የመንገድ ግንባታ በሁለት ተርም የሚሰራ ሲሆን የመጀመሪያው ዳማ ጵዝጎ ሜላ የ23 ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ የአፈር ቆረጣ ስራ ተጠናቆ ወደ ስትራክቸር ስራ ተገብቷል ብለዋል።
አያይዘውም የመንገዱ አካል የሆነው ማላንጋ፣ ኤልሴና ላስቴ የሚገኙ የሦሥት ወንዞች ላይ የድልድይ ስራ አዲኮ ከሚባል ተቋራጭ ጋር ስምምነት በመግባት ጨረታው ተጠናቆ ወደ ስራ የተገባ ሲሆን ለግንባታውም 88,766,317 ሚ ብር በላይ ወጪ ተመድቦለታል በማለት ገልፀዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ሣውላ ዲስትሪክት የመንገድ ጥገና ስራዎች አስተባባሪ ኢንጂነር ስለሽ ሽብሩ በበኩላቸው እንደተናገሩት የመንገዱ ስራ ለማህበረሰቡ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን የሚፈታ ስሆን 5 ቀበሌያትን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ብለዋል ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ዳማ -ጵዝጎ- ሜላ ሳይት አስተባባሪ አቶ ስላስ ተስፋዬ እንደገለፁት የዚህ መንገድ ስራ 23 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን በመንገዱ ስራ ትልልቅ የወንዝ ላይ ድልድይዎችን በመያዝ የሚሰራ ይሆናል ብለዋል።
በአካባቢው ነዋሪ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች እንደተናገሩት ለሠው ልጆች ከሚያስፈልጉ መሠረተ ልማቶች ውስጥ አንዱ መንገድ ሲሆን ለዘመናት ይህንን ልማት በማጣት ብዙ የመከራ ጊዜያትን እንዳሳለፉ ተናግረው አሁን ተጀምሮ እየተሰራ ያለው መንገድ ጥያቄያቸውን በመመለስ ምራታቸውን ያለ ችግር ወደ ገበያ እንዲያቀርቡ እንደሚረዳቸው ተናግረዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ሣውላ ዲስትሪክት በጎፋ ዞን የሜላ -ጵዝጎ -ዳማ- ቆርጳ -በቶ የመንገድ ሰራ በፍጥነት እየተሰራ ይገኛል።