ጎፋ ዞን በተፈጥሮ የታደለ፣ ለግብርና ሥራ እጅግ ምቹ የሆነ ስነ-ምህዳር ያለው አካባቢ ነው።
በህዝቡ ዘንድ “በጎፋ ምድር ከጨው ውጪ ሁሉም ተዘርቶ ይበቅላል” የሚባለው አባባል የአካባቢውን የመሬት ለምነትና የአየር ፀባይ ተስማሚነት በግልጽ ያሳያል።
ዞኑ በተለይም ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የኤክስፖርት ሰብሎች ምርት በስፋት የሚካሄድበት ከፍተኛ አቅም ያለው አካባቢ ነው።
ቡና፣ ኮረሪማ፣ ሰሊጥ፣ ማሾ እና ቀይ ቦሎቄ በሰፊ ስፋትና በላቀ ጥራት በመመረታቸው ለአርሶ አደሩ የገቢ ምንጭ ከመሆን ባለፈ ለሀገር ኢኮኖሚም ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ።
የጎፋ ህዝብ በትጋትና በፈጠራ ሥራ በመታገዝ የአካባቢውን የግብርና አቅም ወደ ተሻለ ደረጃ እያሸጋገረ ሲሆን፣ ዘላቂ ልማትና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ትልቅ ሚና እየተጫወተ ነው።
ጎፋ ዞን፤ የለምለም ምድር፣ የበረከት መገኛ፣ የኢኮኖሚ እድገት መሰረት!
ጎፋ፤ የግብርና ተስፋ ምድር!