በጎፋ ዞን በአራት ወረዳዎች የውሃ መሠረተ ልማት ተደራሽነትን ለማስፋፋት የሚያግዝ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

የውሃ መሠረተ ልማት አስተዳደርንና የምግብ ዋስትናን የሚያሻሽሉ ፈጠራዎች ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ ።

ሰኔ/12/2018 ዓ.ም

''ስማርት ዋሽ '' የተሰኘ በኢትጵያ የዉሃ መሠረተ ልማት አስተዳደርንና የምግብ ዋስትናን የሚያሻሽሉ ፈጠራዎች ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል ።

የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ፣ ፕሮጀክቱ የውሃ መሠረተ ልማት ተደራሽነትን ለማስፋፋት እየሰራ ያለውን ተግባር አድንቀዋል ።

ፕሮጀክቱ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመረጧቸው አራት ወረዳዎች በጎፋ ዞን እንደሚገኙ ጠቅሰዋል ።

ፕሮጀክቱ የመጠጥና የመስኖ ዉሃ አገልግሎችን በማዘመን ለህብረተሰቡ ኑሮ መሻሻል ዘርፈ ብዙ ስራ እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል ።

የዞኑ መንግስትም አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ከድርጅቱ ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ አስረድተዋል ።

የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ምርምርና ትብብር ምክትል ፕሬዝዳንት ተክሉ ወጋየሁ(ዶ/ር)፣ ዩኒቨርስቲው በበጎ ተግባራት ከተማሰሩ ድርጅቶች ጋር በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል ።

''ስማርት ዋሽ'' የውሃ ግብዓቶችን ለማዘመንና በምግብ ራስን ለመቻል የሚያግዙ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል ።

ዩኒቨርስቲው ከፕሮጀክቱ ጋር በመተባበር በውሃ አጠባበቅና አጠቃቀም ዙሪያ ለማህበረሰቡ የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎችን የእሰራ መሆኑን አብራርተዋል ።

ድርጅቱ የሚያከናወናቸው ተግባራት የውሃ ንፅህናን በማስጠበቅና የመስኖ ውሃ አጠቃቀምን በማዘመን የማህበረሰቡን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት እንደሚረዳ አስረድተዋል ።

በዩኒቨርሲቲው የዉሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፍክ ዳይሬክተር ኢ/ር ታምሩ ተሰሜ (ዶ/ር)፣ዩኒቨርስቲው ለስራው መዘመን የሚረዱ በቴክኖሎጂ የታገዙ ስልጠናዎችን በመስጠት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል ።