ኢትዮጵያዊያን በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለዴሞክራሲ ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል - ማህሙድ አሊ ዩሱፍ
ሰኔ 16/2018 ዓ.ም
ኢትዮጵያዊያን በስኬት ባካሔዱት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለዴሞክራሲ ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህመድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ።
ሊቀመንበሩ በኢትዮጵያ ለተካሄደው የተሳካ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።
በምርጫው ላሸነፈው የብልጽግና ፓርቲ እና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የምርጫው ሂደት ኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት መሰረት እንዲሆን ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ ያሳየውን ሙያዊ ብቃት እና ቁርጠኝነት ማድነቃቸውን ከአፍሪካ ህብረት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሊቀመንበሩ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን በታማኝነት፣ ሰላማዊ እና ግልጽነት ባለው የምርጫ ሂደቶችን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኑንም መግለፃቸውን የኢዜአ መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያዊያን በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለዴሞክራሲ ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል - ማህሙድ አሊ ዩሱፍ