የጎፋ ዞን ግብርና መምሪያ የ2017/18 ዓ/ም ግብርና ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2018/19 ዓ/ም የመኸር ዕቅድና የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ መድረክ የመዋቅር የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በሣውላ ከተማ አካሂዷል።
የጎፋ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ደግፌ እንደተናገሩት የግብርናው ዘርፍ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣትና ድህነትን በመቀነስ ረገድ ወሳኝ ድርሻ ያለው በመሆኑ በዕቅድ መመራትና አፈፃፀሙን መገምገም እንዳስፈለገ ገልፀዋል።
አክለውም በ2017/18 ዓ/ም ግብርና ዕቅድ አፈፃፀም በአዝርዕት ሰብሎች፤ሆርቲካልቸር፣ነባር እንክብካቤ ከታቀደው 91,034 ላይ 91,941 በመፈፀም 100% ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል።
አቶ ዳንኤል አያይዘው በአፈፃፀሙ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ያሉ ክፍተቶችን በመቅረፍ በሙሉ ፓኬጅ የመጠቀም ባህልን በማሳደግ በቀጣይ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ይሰራል ብለዋል።
በቀጣይ እንደከዚህ ቀደሙ የአረንጓዴ አሻራ ውጤታማነት በቀጣይ ስራዎችን በህዝብ ማዕበል በማጀብ እንዲሁም ለክትትልና ቁጥጥር እንዲመች በሣይት ልየታና በመረጃ ቋት በማስገባት ለውጤት ይሰራል ብለዋል።
የጎፋ ዞን ግብርና መምሪያ አደጋ ስጋት ኃላፊ አቶ ያዕቆብ ዘካሪያስ በበኩላቸው እንደተናገሩት የግብርና ስራ በዋናነት በምርት ራስን በመቻል ከተረጂነት ለመውጣት መስራት በመሆኑ በትብብርና በቅንጅት እንሰራለን ብለዋል።
አቶ ያዕቆብ አያይዘው በየመዋቅሩ በአደጋ ጊዜ ቀድሞ ለመድረስና ራስን ለመቻል በህዝብ በማሳረስ ምርት እየተሰበሰበ እንዳለና ግንዛቤው ግን በቂ እንዳልሆነ ገልፀዋል።
በየመዋቅሩ ከተረጂነት ለማላቀቅ ሀብት አግኝተው የተሸጋገሩ የማህበረሰብ ክፍሎች ወደ ቀደመ ድኅነታቸው እንዳይመለሱ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግና በቀጣይ ሌሎችንም በማሸጋገር ከተረጅነት መላቀቅ አንደኛ ግባችን አድርገን እንሰራለን ብለዋል።
ከየመዋቅሮች የመጡ አመራርና ባለሙያዎች በሰጡት ሃሳብ ባለፈው አፈፃፀም በጠንካራ ጎን የተፈፀሙትን በማስቀጠል በቀጣይ የታቀዱትን ለመፈፀም የጋራ ስምምነት ላይ በመድረስ መድረኩ ተጠናቋል።
የጎፋ ዞን ግብርና መምሪያ የ2017/18 ዓ/ም ግብርና ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2018/19 ዓ/ም የመኸር ዕቅድና የአረንጓዴ አሻራ ተከላ ንቅናቄ መድረክ በሣውላ ከተማ ተካሂዷል