"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል በጎፋ ዞን ጋልማ ከተማ የ2018/19 ዓ.ም የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል።

ሰኔ 19/2018 ዓ.ም

በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ በሚል መሪ ቃል ዞናዊ የክረምት ወራት የወጣቶች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መረሃ ግብር በጋልማ ከተማ ከፍተኛ የክልል፣የዞን፣የከተማ እና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በጋልማ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የመረዳዳት፣ የመተባበርና የአንድነት እሴቶችን በማጠናከር ማህበረሰቡ ለአካባቢውና ለሀገሩ እድገት በተግባር እንዲያበረክት የሚያስችል የዜግነት ኃላፊነት መገለጫ ነው።

በዚህ የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ ንቅናቄም በትምህርት፣ በጤና፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በማህበራዊ ድጋፍና በሌሎች የልማት መስኮች ሰፊ ተሳትፎን ለማሳደግ በልዩ ትኩረት ይሰራል ተብሏል።

በመሆኑም የሁላችንም ትናንሽ በጎ ተግባራት ሲደመሩ ለሀገራችን ብሎም ለአከባቢያችን ትልቅ ለውጥና ከፍታ እንደሚያመጡ ባለፉት ጊዚያቶች የተሰሩ ስራዎች አመላካች ናቸው።

ስለዚህ ሁሉም ዜጎች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በንቃት በመሳተፍ የመረዳዳትና የመተሳሰብ ባህላችንን ይበልጥ እናጠናክር።

በዘንድሮው የክረምት ወራት በ18 የትኩረት መስኮች 148,919 ወጣቶችን ለማሳተፍ መታቀዱ ተገልጿል።

በመርሃ ግብሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቦጋለ ፈይሳ፣ የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ፣የጎፋ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ጋሻያለው ገላ፣ የዞኑ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት፣ የወረዳና የከተማ አስተባባሪዎች፣ እንዲሁም ሌሎች አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በስፋት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

#በጎነት_ለኢትዮጵያ_ከፍታ
#የበጎ_ፈቃድ_አገልግሎት