በጎፋ ዞን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በ online በሣውላ ማዕከል መሰጠት ተጀመረ።
‎
‎ሰኔ 23/2018 ዓ.ም
‎
‎በጎፋ ዞን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በ online በሣውላ ማዕከል መሰጠት ተጀመረ።
‎
‎በማስጀመሪያው ላይ የጎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለን ጨምሮ፣ የሣውላ ከተማ አስተዳደር ከፍኛ አመራሮች ተገኝተው ለተማሪዎች መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
‎
‎የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች እየተፈተኑ ላሉ ተማሪዎች ስኬት የጥረት እና የትህጋት ውጤት በመሆኑ ተማሪዎች ከአላስፈላጊ የስነ-ልቦና ጫና በመላቀቅ ፈተናውን መቀበል እንዳለባቸው ተናግረዋል።
‎
‎በስተመጨረሻ ለተፈታኝ ተማሪዎች መልካም ውጤት ተመኝተዋል።
‎