🌱 "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ በጎፋ ዞን በይፋ ተጀምሯል!

በዘንድሮው የክረምት ወቅት "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል በዞኑ ከ23 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ለመትከል የተዘጋጀው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በይፋ ተጀምሯል።

በዚሁ መሠረት በጎፋ ዞን በኦይዳ ወረዳ ከፍተኛ የዞንና የወረዳ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ ተቋማት አመራሮች እና ህብረተሰቡ በተገኙበት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በይፋ ተካሂዷል።

በዞኑ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎችና ከተሞች የተጀመረው ይህ የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ በቀጣይ ቀናትም በሰፊው የህዝብ ተሳትፎ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

በተለይም በአንድ ጀምበር ብቻ በጎፋ ዞን በሁሉም መዋቅሮች ከ8 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ለመትከል የተቀመጠው ግብ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለደን ልማት፣ ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም እና ለቀጣይ ትውልድ አረንጓዴ አካባቢን ለማስተላለፍ የሚያበረክተውን አስፈላጊ አስተዋፅኦ ያሳያል።

"ዛሬ የምንተክለው ችግኝ የነገው ተስፋ ነው!"