"ጠንካራ ተቋማት የሚገነቡት በጠንካራ አባልነት፣ በጋራ ተሳትፎና በዘመናዊ አሰራር ነው!"አቶ ቦረና ቦላዶ
ሐምሌ 2/2018 ዓ.ም
የጎፋ ዞን ልማት ማህበርና የጎፋ ዞን ቀይ መስቀል ማህበር ዞናዊ የአባላት ማፍራትና የሀብት ማሰባሰቢያ ንቅናቄ መድረክ በሣውላ ከተማ አካሂደዋል።
በመድረኩ የጎፋ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካና ሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ቦረና ቦላዶ፣ የልማት ማህበሩና የቀይ መስቀል ማህበሩ በሰው ኃይል የተደራጁ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፉ እና ግልጽ አሰራር የዘረጉ ተቋማት በመሆን ለሕብረተሰቡ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
በዞኑ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ አባላትን በማፍራት፣ የአባልነት መታወቂያ ስርጭትን በማጠናከርና የአባልነት መዋጮን በሥርዓት በማሰባሰብ የተቋማቱን ዘላቂ የፋይናንስ አቅም ለማጎልበት በሁሉም መዋቅሮች የተቀናጀ ሥራ እንደሚከናወን ጠቁመዋል።
አቶ ቦረና አክለውም የጎፋ ዞን ልማት ማህበርና የቀይ መስቀል ማህበርን በቴክኖሎጂ በማጠናከር ተወዳዳሪና ውጤታማ ተቋማት ለማድረግ በትኩረት ይሰራል ስሉም ተናግረዋል።
የጎፋ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ይሁን ደምሴ በበኩላቸው፣ የጎፋ ዞን ልማት ማህበርና ቀይ መስቀል ማህበርን መደገፍ የሁሉም ዜጎች የጋራ ኃላፊነት መሆኑን ገልጸው፣ ሁሉም አመራርና ህብረተሰብ የአባልነት ግዴታውን በመወጣት ለማህበራቱ መጠናከር የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
በመድረኩ የጎፋ ዞን ልማት ማህበር ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ነፃመት ገመዳ እና የጎፋ ዞን ቀይ መስቀል ማህበር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢያሱ ጣሰው የተቋማቱን የሪፎርም ሥራዎች፣ የአባላት ማፍራት፣ የገቢ ምንጮችን ማስፋትና ሰብዓዊ አገልግሎትን የበለጠ ለማጠናከር የተያዙ እቅዶችን አቅርበዋል።
የአባላት ማፍራት፣ የገቢ ምንጮችን ማስፋት፣ የተቋማቱን ዲጂታል አሰራር ማጠናከርና የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማሳደግ የተቋማቱን ተቋማዊ አቅም የበለጠ ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰራም ገልጸዋል።
መድረኩ የልማት ማህበሩንና የቀይ መስቀል ማህበሩን የአባልነት መሰረት በማስፋት፣ የገቢ አቅማቸውን በማሳደግ እና ለሕብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት የሚሰጡ ጠንካራ ተቋማት ለመገንባት የጋራ ቁርጠኝነት የተረጋገጠበት መሆኑን ተሳታፊ አካላት ገልፀዋል።
በንቅናቄ መድረኩ የዞኑ አመራሮች፣ የክልልና የዞን ተቋማት ኃላፊዎች፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ የልማት ማህበርና የቀይ መስቀል ማህበር ሥራ አስኪያጆች እንዲሁም የሚዲያ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
የጎፋ_ዞን_መንግስት_ኮሚዩኒኬሽን_አገልግሎት
ጠንካራ ተቋማት የሚገነቡት በጠንካራ አባልነት፣ በጋራ ተሳትፎና በዘመናዊ አሰራር ነው!"አቶ ቦረና ቦላዶ