በጎፋ ዞን በራስ አቅም የሰብዓዊ ድጋፍ ሀብት ማሰባሰብ ንቅናቄ በዞን ማዕከል በይፋ ተጀመረ
በጎፋ ዞን የዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማጠናከር፣ በችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች በራስ አቅም ፈጣን የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ እና የማህበረሰብ መተጋገዝን ለማጎልበት የተጀመረው የሀብት ማሰባሰብ ንቅናቄ በዞን ማዕከል በይፋ ተጀምሯል።
በዞን ማዕከል በተካሄደው የማስጀመሪያ መርሃ ግብር የዞኑ አመራሮች 30 ኩንታል በቆሎን በጋራ በማበርከት ዘመቻውን በይፋ አስጀምረዋል። በተጨማሪም ገንዘብና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች በመሰብሰብ ለተጎጂ ዜጎች የሚደረገውን ድጋፍ ለማጠናከር ተግባራዊ ሥራዎች ተጀምረዋል።
ዘመቻው በዞን ማዕከል ብቻ ሳይወሰን በወረዳዎች፣ በከተሞች፣ በቀበሌዎችና በሌሎች መዋቅሮች ጭምር በተቀናጀ ሁኔታ እየተካሄደ ሲሆን፣ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የአቅማቸውን ያህል በመሳተፍ የመተጋገዝ ባህልን እንዲያጠናክሩ ጥሪ ቀርቧል።
የሚሰበሰበው ሀብት ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመፍታት እና የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ እንደሚውል የተገለጸ ሲሆን፣ የሀብት ማሰባሰብ ሥራውም በየደረጃው ባሉ መዋቅሮች ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በጎፋ ዞን በራስ አቅም የሰብዓዊ ድጋፍ ሀብት ማሰባሰብ ንቅናቄ በዞን ማዕከል በይፋ ተጀመረ