ዘመናዊ የእርሻ ቴክኖሎጂ የጎፋ ዞንን የግብርና ልማት ወደ አዲስ ምዕራፍ እያሸጋገረ ነው
በጎፋ ዞን የ2018/19 የመኸር ምርት ዘመን ዕቅድን በተሳካ ሁኔታ ለማሳካት የእርሻ መካናይዜሽንና ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም በዞኑ ወረዳዎች በስፋት እየተተገበረ ሲሆን፣ የግብርና ልማቱን ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ ተጨባጭ ውጤቶች እየተመዘገቡ ነው።
በዚህ ሂደት የዛላ ወረዳ በሜላ ቃውሣ ቀበሌ የ2018/19 የመኸር ምርት ዘመን የሜካናይዜሽን እርሻ ሥራን በይፋ በማስጀመር ለሌሎች ወረዳዎችም አበረታች ተሞክሮ ሆኗል።
የዛላ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አንበስ ሀነና በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ የግብርና ሥራን በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በሜካናይዜሽን መደገፍ የመሬት ዝግጅትን በወቅቱ ለማከናወን፣ የጊዜና የጉልበት ብክነትን ለመቀነስ፣ የምርትና የምርታማነት ዕድገትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም የሜካናይዜሽን አጠቃቀም ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር፣ በምግብ ራስን ለመቻልና ዘላቂ የግብርና ልማትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና እንዳለው አስገንዝበዋል።
በጎፋ ዞን በዘንድሮው የመኸር ምርት ዘመን የትራክተር አገልግሎት፣ የዘመናዊ የማረሻ መሳሪያዎች አጠቃቀምና ሌሎች የግብርና ቴክኖሎጂዎች በስፋት ወደ ተግባር በመግባታቸው ገበሬዎች ሥራቸውን በወቅቱ በማከናወን ከፍተኛ ምርት ለማምረት እድል እያገኙ ነው።
በመሆኑም የእርሻ መካናይዜሽንን በዞኑ ሁሉም ወረዳዎች በማስፋፋት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግሩን በማጠናከርና የገበሬዎችን ተሳትፎ በማሳደግ የ2018/19 የመኸር ምርት ዕቅድን ከግብ ለማድረስ ሥራዎች በተጠናከረ ሁኔታ እየተከናወኑ ነው።
የጎፋ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት
ዘመናዊ የእርሻ ቴክኖሎጂ የጎፋ ዞንን የግብርና ልማት ወደ አዲስ ምዕራፍ እያሸጋገረ ነው