የክልሉ ጤና ቢሮ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የጤና ልማትና ኢንቨስትመንት አፈፃፀምና በ2019 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ ዙሪያ የምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል

ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት የጤና ልማትና ኢንቨስትመንት እቅድ አፈፃፀምና በ2019 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በአርባ ምንጭ ከተማ የምከክር መድረክ እያካሄደ ነው።

በመድረኩ የ2018 በጀት አመት አፈፃፀምና የቀጣይ በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ ቀርቦ ምክክር እንደሚደረግበት ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል።

በመርሃ ግብሩ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የወላይታ ሶዶ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዞን አስተዳዳሪዎች፣ የሪጂዮ ፖሊስ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች የጤና መዋርቅ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛል።