የጎፋ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር መርሃ ግብር 13ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል።

ሣውላ!ነሐሴ 3/2018 ዓ.ም

የጎፋ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው መደበኛ ጉባኤ የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ፣የምክር ቤት አባላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

በጉባኤው መክፈቻ በጀት ዓመቱ በዞኑ የተመዘገቡ ስኬቶችን የሚያሳይ ዶክመንተሪ ቪዲዮ እና የፎቶ አውደርእይ ተዘጋጅቶ የምክር ቤት አባላት እና የክብር እንግዶች ተመልክተዋል።

በጉባኤው የተለያዩ የአፈጻጸም ሪፖርቶች፣ የ2019 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅዶች እና የበጀት ረቂቅ አዋጆች ቀርበው በምክር ቤቱ አባላት ውይይት እንደሚደረግባቸው ይጠበቃል።