‎በጎፋ ዞን የ2018 ዓ/ም የፓርቲና የመንግስት ሥራዎች አፈፃፀም ማጠቃለያ ግምገማ እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የሚመክር ዞናዊ የከፍተኛ አመራሮች መድረክ በሣውላ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
‎
‎ሣውላ፦ነሀሴ5/2018 ዓ/ም
‎
‎በጎፋ ዞን የ2018 ዓ/ም የፓርቲና የመንግስት ሥራዎች አፈፃፀም ማጠቃለያ ግምገማ እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የሚመክር ዞናዊ የከፍተኛ አመራሮች መድረክ የክልሉ የፕላን ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍቃደስላሴ ቤዛ ጨምሮ የዞን ስራ አስተባባሪዎች፤የዞኑ የመምሪያና ጽ/ቤት ኃላፊና ምክትል ኃላፊዎች እንዲሁም የከተማና የወረዳ ስራ አስተባባሪዎች በተገኙበት በሣውላ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
‎
‎በመድረኩ የጎፋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጋሻያለው ገላ በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ የፓርቲ እና የመንግስት ስራዎች የአፈፃፀም ሰነድ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።
‎
‎በመድረኩ እንደተገለፀው ሀገራችን ኢትዮጵያ ሁሉንም አካታች የሆነ ዴሞክራስ ስርዓት እየገነባች ትገኛለች።በዚህ ስርዓት የመደመር መንግስት ፓርቲያችን ብልፅግና በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
‎
‎በሌላ መንገድ ከምርጫ በፊት ከመጋቢት እስከ መጋቢት በሚል በትብብርና በቅንጅት ምርጫ እንዲሳካ ትልቅ አስተዋፅኦ አድርገናል ብለው ምርጫን በሠላማዊ መንገድ ካሳለፍን በኋላ ከምርጫው ማግስት ጠንካራ መንግስት በሚል መርህ የተሰሩ ስራዎችን የፓርቲና የመንግስት የስራ አፈፃፀሞችን በተገቢው መንገድ በመገምገም ለዛሬው ማጠቃለያ መድረክ ደርሰና ሲሉ ተናግረዋል።
‎
‎ዞናችንን የሠላምና የልማት ተምሳሌት እንድትሆን ለመስራት ሀደራ የተቀበልን ትውልዶች በመሆናችን ለቀጣይ ትውልድ መልካም ዕሴቶችን አሻራ ለማስቀመጥ ብዙ ይጠበቅብናል በማለት አፅንኦት ሰጥተዋል።
‎