የፌዴራል ጤና ሚኒስትር የቲቢ እና ስጋ ደዌ ኤክስፐርት ወ/ሮ መቅደስ በቀለ የተመራ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ስር በሚገኙ ማረሚያ ተቋማት የቲቢ እና አጠቃላይ የበሽታ መከላከል ስራ ያለበትን ደረጃ ድጋፋዊ ክትትል አደረጉ
የፌዴራል ጤና ሚኒስትር የቲቢ እና ስጋ ደዌ ኤክስፐርት ወ/ሮ መቅደስ በቀለ ጠቅለል ያለ ግብረ-መልስ በመስጠት የቀጣይ አቅጣጫም አስቀምጠዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የቲቢ፣ሥጋ ደዌና ሌሎች የሳንባ በሽታዎች ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ታዲዮስ ጤና እንደገለፁት በትላንትናው ዕለት በ7ቱ ማረሚያ ፖሊስ ተቋማት በዘመናዊ ዲጂታል X-Ray Machine ታግዞ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
በመጀመሪያ ቀን 3455 የህግ ታራሚዎች የቲቢ ልየታ ምርመራ ተደርጎ በቁጥር 05 /አምስት/ የቲቢ በሽታ ምልክት ያለባቸው የህግ ታራሚዎች ተገቢውን ህክምና እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑንም አስተባባሪው ጠቁመዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ብርቱካን መንግስቱ በበኩላቸው ኮሚሽኑ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት አቻ ለአቻ ምክር፣ የቲቢ ታማሚዎችን የድጋፍ አገልግሎት ለማጠናከር፣ግንዛቤ ለማሳደግና የቲቢ ህክምና እንዲያገኙ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
በሽታው በቀላሉ ተላላፊ መሆኑን ተከትሎ በታራሚዎች ላይ ከፍተኛ የጤና ችግር ሊያስከትል ስለሚችል በዘመቻና በመደበኛ ፕሮግራም በተደረገ አሰሳ የቲቢ በሽታ ተጠቂዎችን መለየት መቻሉንና ህክምና እያገኙ ያሉ መኖራቸውንም ጠቁመዋል።
እስከ አርብ በሚቆየው የዘመቻ ስራ የክልሉ ጤና ቢሮ፣ የዞን ጤና መምሪያ እና የማረሚያ ተቋማት ባለሙያዎች እየተሳተፉ እንደሚገኝ ተመላክቷል።