የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች መሎ ኮዛ ወረዳ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ በዶ/ር መርሁን ፍቅሩ የተመራው የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች ቡድን፣ የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለን ጨምሮ፣ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት መሎ ኮዛ ወረዳ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።

ከፍተኛ አመራሮቹ ወደ ወረዳው ሲደርሱ የወረዳው አመራሮችና የማኅበረሰቡ ተወካዮች እና ቀደማቅ አቀባበል ተቀብለዋቸዋል።

አመራሮቹ በወረዳው በሚያደርጉት የሥራ ጉብኝት በክረምት በጎ ፈቃደኝነት መርሐ ግብር የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታን በይፋ የማስጀመር ሥራ እንደሚያከናውኑ ይጠበቃል።

በተጨማሪም ከአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ ጋር በተያያዘ የቡና ችግኝ ተከላ በማከናወን የአካባቢ ጥበቃን፣ የቡና ልማትንና የዘላቂ ልማት ጥረቶችን የሚያጠናክር ተግባር እንደሚያከናውኑ ተጠቅሷል።

የሥራ ጉብኝቱ በወረዳው የሚከናወኑ የልማት፣ የማኅበራዊ ድጋፍና የአረንጓዴ አሻራ ተግባራትን በመጎብኘትና በመገምገም ቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎችን ለማጠናከር ያለመ ነው።