የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ የወላይታ ብሔረሰብ "የጊፋታ"በዓል ላይ እንዲታደሙ የቀረበላቸውን ጥሪ በደስታ ተቀበሉ
ሣውላ፣ ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም
የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ የወላይታ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ የጊፋታ ክብረ በዓል ላይ እንዲታደሙ ከወላይታ ዞን አስተዳደር የቀረበላቸውን የክብር ጥሪ በደስታ ተቀብለዋል።
በወላይታ ዞን ምክትል አፈ-ጉባኤ የተመራው ልዑካን ቡድን በጎፋ ዞን ሣውላ ከተማ በመገኘት ለጎፋ ዞን አስተዳደር የጊፋታ ክብረ በዓል የግብዣ ጥሪውን አቅርቧል።
በወቅቱም የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ የቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው፣ ለመላው የወላይታ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል የጊፋታ እንኳን አደረሳችሁ በማለት “ዮ! ዮ! ጊፋታ!” ሲሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በዓሉን በጋራ ለማክበርና አዲሱን ዘመን በአንድነት ለመቀበል የቀረበውን የግብዣ ጥሪ በመቀበላቸውም፣ የሁለቱ ተጎራባች ሕዝቦች በታሪክ፣ በባህልና በማህበራዊ ግንኙነት ያላቸውን ትስስርና አብሮነት የበለጠ ለማጠናከር በዓሉ ጠቃሚ አጋጣሚ መሆኑ ተገልጿል።
ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ የጊፋታ በዓል በዩኔስኮ (UNESCO) የማይዳሰስ የባህል ቅርስ ሆኖ የተመዘገበበትን ማግስት የሚከበር መሆኑ የዘንድሮውን በዓል ይበልጥ ልዩና ታሪካዊ እንደሚያደርገው ገልጸዋል።
በዚህም መሠረት፣ “የጊፋታ ብሔረሰባችን ረጅም ዘመን” በሚል መሪ ቃል የወላይታ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ የጊፋታ በዓል በመጪው መስከረም 10/2019 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልልና ከሌሎች ክልሎች በሚገኙ እንግዶች ተሳትፎ በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበር ተገልጿል።
ዮ! ዮ! ጊፋታ! እንኳን ለአዲሱ ዘመን አደረሳችሁ!
የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ የወላይታ ብሔረሰብ "የጊፋታ"በዓል ላይ እንዲታደሙ የቀረበላቸውን ጥሪ በደስታ ተቀበሉ