የጎፋ ዞን ትምህርት መምሪያ የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተና ኦረንተሽን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በሣውላ ከተማ በመስጠት ይገኛል።
የጎፋ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሞገስ መኩሪያ እንደገለፁት እንደ ዞን የ6ኛና የ8ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና በተሻለ መልኩ ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በልዩ ሁኔታ መሰራቱን ተናግረዋል።
አያይዘውም እኔደ ዞን የ6ኛ ክፍል ፈተና በ279 ትምህርት ቤቶች የሚሰጥ ሲሆን በአጠቃላይ ወንድ,5783 ሴት ,6813 ድምር 12,596,ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ጠቁመዋል።
የ8ኛ ክፍል ፈተና በ228 ትምርት ቤቶች ወንድ ,3932 ሴት ,4237 ድምር,8169 የሚሆኑ ተማሪዎች እንደምፈተኑ አክለዋል።
የ2018 የ6ኛ ክፍል እና የ8ኛ ክፍል ፈተና እያንዳንዱ ባለድርሻ አካል በትኩረት እንዲመራ መልክት አስተላልፏል።
የተማሪዎች የልፋታቸው ውጤት የሚገለጽበት የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ስላለን ከኩረጃ ነፃ በሆነ መንገድ የፈተና ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ በድስፕሊን እንድመራ አጥብቀው አሳስበዋል ።
በመጨረሻም እያንዳንዱ መዋቅር የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተና ከዞን ማዕከል በሰላም በጥበቃ ታጅቦ እንድገባ ተደርጉዋል።
በመረሃ ግብሩ ከወረዳና ከተማ አስተዳደር የትም/ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የፈተና ክፍል ኃላፊዎች ፣ፀጥታ አስከባሪዎች ጨምሮ የትምህርት መምሪያ አመራሮች እና ማኔጅመንት አካላት ተገኝተዋል።