የመጀመሪያው የፖለቲካ ሥልጣን ለሰፊው ማኅበረሰብ ለጋራ ጥቅም እንደሚውል ሲታመን ነው። ሁለተኛው ደግሞ መልካም አስተዳደር ማስፈን ግቡ ያደረገ ሥርዓት ሲኖር ነው። ለዚህም ፈጣን ማኅበረሰባዊና ሥርዓታዊ ለውጦችን ማድረግ ይጠይቃል፡፡ እነዚህ ለውጦች በፍጥነት ካልተመሩ የተለያዩ የፖለቲካ ቡድኖችና የማኅበረሰብ ክፍሎች ነጣጣይ አጀንዳ በመፍጠር ስለሚጠመዱ፣ የፖለቲካ አለመረጋጋት በሀገሩ ይንሠራፋል፡፡